Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትምህርት ዘርፉን ለማጠናከር ድጋፌና አጠናክሬ እቀጥላለሁ አለ ሪች ፎር ቼንጅ

ትምህርት ሚኒስቴር እና ሪች ፎር ቼንጅ የትምህርት ዘርፉን ይበልጥ ለማጠናከር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር መቅድም ጉልላት እንዳሉት ÷ ሪች ፎር ቼንጅ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ጥቀጥላል፡፡

በዚህ መሰረትም የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ እንዲሁም የሥራ ፈጠራን በማበረታታት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ በዋናነትም በማሕበረሰቡ ወስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችሉ ሃሳቦች ያሏቸውን ሥራ ፈጣሪዎችን እንደሚያበረታታ አስረድተዋል፡፡

ለአብነትም የቆሻሻን ሃብትን በአግባቡ በማስወገድ ወደ ንግድ ሥራ ሃሳብ የቀየሩ ሥራ ፈጣሪዎችን እየደገፈ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡

የሪች ፎር ቼንጅ ሲኒየር ፕሮጀክት ማኔጀር ኤልሳቢት ጸጋዬ በበኩላቸው÷ ድርጅቱ የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን ክህሎት በማጠናከረ፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግና የገበያ ትስስር በመፍጠር ወደ ሥራ እንዲገቡ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ከማዕከል ሩቅ ሆኑ አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡፡

የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማሳድገ፣ የትምህርት ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እና የትምህርት ግብዓት አቅርቦትን ለማሳለጥ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሪች ፎር ቼንጅ በ”ግሪን ኢኖቬሽን” ዘርፍ የተሰማሩ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ሃሳባቸውን ለባለሙያ ዳኞችና ባለሃብቶች ያቀረቡበት መድረክ ተካሂዷል፡፡

Exit mobile version