አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አልጄሪያ እና ቡርኪና ፋሶ አሸንፈዋል።
በምድብ አምስት ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ በአልጀሪያ ኢኳቶሪያል ጊኒን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
የአልጀኢሪያን የማሸነፊያ ግቦች ኢብራሂም ማዛ፣ ፋሬስ ቻይቢ እና ዚነዲን ቤላይድ ሲያስቆጥሩ ኤሚሊዮ ንሱ የኢኳቶሪያል ጊኒን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል።
እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ ሱዳንን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች።
በጨዋታው ላሲና ትራኦሬ እና አርሴን ኩዋሲ የቡርኪናፋሶን ግቦች አስቆጥረዋል።
ምድቡን አልጄሪያ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ ስታጠናቅቅ ቡርኪና ፋሶ በስድስት ነጥብ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።
ምሽት 4 ሰዓት ላይ የምድብ ስድስት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ጋቦን ከኮትዲቯር እንዲሁም ሞዛምቢክ ከካሜሩን ይጫወታሉ።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

