Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ የበዓል ፍጆታ እቃዎች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዓላትን ተከትሎ የሚከሰቱ የምርቶችን ዋጋ ጭማሪ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ፡፡

የቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ መጪዎቹን የገናና ጥምቀት በዓላትን ተከትሎ በምርቶች ላይ እጥረትና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ለዚህም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ግብረ ኃይል መቋቋሙን አመልክተዋል፡፡

በተለይም ግንዛቤ በመፍጠር ከበዓላት ጋር ተያይዞ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር እና የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በብዛት ወደ ገበያዎች ከአምራቾችና ከአቅራቢዎች በስፋት እንዲቀርብና የገበያ ትስስር እንዲፈጠር እየተደርገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም የአስተዳደር እርከን የበዓል ገበያዎችን የማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ በመሆኑ ሕብረተሰቡ ተረጋግቶ እንዲሸምትና የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን እንዲጠቁም ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል በየደረጃው ያሉ የሕብረት ሥራ ዩኒየኖችና መሰረታዊ ማሕበራት ለበዓል ገበያ ተፈላጊ ምርቶችን በተለይም ጤፍ፣ ሽንኩርት፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ ቲማቲም፣ የእርድ እንስሳት፣ ፍራፍሬና ሌሎች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version