Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በድሬዳዋ ንጹህ ያልነበረን መሬት ወደ አረንጓዴ ሥፍራ የቀየረው ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘውን ባዶ እና ንጹህ ያልነበረን መሬት ወደ አረንጓዴ ሥፍራ በመቀየር ለከተማ አስተዳደሩ አስረክቧል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የሲሲቢኤ በኢትዮጵያ አመራሮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክቱ ለማሕበረሰቡ አገልግሎት የሚውል የመፀዳጃ እና የመታጠቢያ ቤት፣ የእግረኛ መንገድ፣ የቡና እና ሸቀጣ ሸቀጥ ኪዮስኮችን እንዲሁም የአረንጓዴ ሥፍራን ያካተተ ነው፡፡

ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ (ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ) ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እና ለማበልጸግ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየቀረጸ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በዚህ መሰረትም በድሬዳዋ ከተማ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ያልዋለ እንዲሁም ንጹህ ያልነበረን መሬት ወደ አረንጓዴ ሥፍራ በመለወጥ ለከተማዋ አስተዳደሩ በማስረከብ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

ተቋሙ አካባቢውን በማደስ፣ መሬቱን በማስተካከል፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የማሕበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እና ንጹህ አካባቢን ለመፍጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ለማሕበረሰቡ አገልግሎት የሚውል የመፀዳጃ እና የመታጠቢያ ቤት፣ የእግረኛ መንገድ፣ የቡና እና ሸቀጣ ሸቀጥ ኪዮስኮችን እንዲሁም የአረንጓዴ ሥፍራን አካትቷል፡፡

ይህም ለአካባቢው ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ ዕድልን ከመፍጠር ባለፈ ትልቅ ኩራት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የመፀዳጃ እና የመታጠቢያ ቤት ክፍሎች ለወንዶች፣ ለሴቶች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች በሚመች መልኩ የተሰሩ ሲሆን ÷ ይህም የድርጅቱን አካታችና ተደራሽነት የሚያረጋግጥ ነው።

የወንዝ መውረጃውን ተከትሎ ም በክረምት ወቅት የሚመጣ የዝናብ ጎርፍ እና የቆሸሸ ውሃ እንዳይጠራቀም የሚከላከል ግድግዳ ተገንብቷል።

ፕሮጀክቱን የከተማ አስተዳደሩ ከተረከባ በኋላ በአካባቢው የሚገኙ ሥራ አጥ ነዋሪዎችን በመለየት በሃላፊነት እንዲጠብቁት እና እንዲያስተዳድሩት እንደሚያደርግ ተጠቅሷል፡፡

Exit mobile version