አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ በ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ወጪ የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክት ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የውሃ ና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ሚሊዮን በቀለ (ኢ/ር) እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ሚሊዮን በቀለ (ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክቱ የሚገነባው ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በቀን ከ400 ሺህ እስከ 950 ሺህ ሊተር ቆሻሻን ማጣራት እንደሚያስችል ነው የገለጹት፡፡
በ22 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፕሮጀክቱ ÷ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ሃላፊዋ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በጸሃይ ጉሉማ

