Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዓልን ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መጪውን የገና በዓል ተከትሎ አላስፈላጊ የተለየ ዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ መጪውን የገና በዓል ተከትሎ የምርት አቅርቦትና የቁጥጥር ስራ በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰራ ነው፡፡

በዓልን ምክንያት በማድረግ የተለየ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ግብረሃይል በማቋቋም እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች በተሻለ ሁኔታ እየቀረቡ ነው ብለዋል፡፡

ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሽንኩርት እና ዶሮን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች በስፋት እየቀረቡ መሆኑን ጠቁመው፤ በሰንበት ገበያዎች ላይ ከመደበኛው ጊዜ በተሻለ ምርት እንዲቀርብ ተደርጓል ነው ያሉት።

ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከግብርና ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በማቴዎስ ፈለቀ

 

Exit mobile version