Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 23 ሺህ በልጧል

አዲስ አበባ ፣ነሃሴ 15፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ23 ሺህ በልጧል፡፡

በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 1ሺህ 829 ሰዎች ውስጥ 1ሺህ18 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ በአጠቃላይም በመዲናዋ 23ሺህ 120 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

ይህንን ተከትሎም ቢሮው በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።

በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ 178 ሰዎች ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣128 ሰዎች ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፥144 ሰዎች ከልደታ ክፍለ ከተማ፣131 ሰዎች ደግሞ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ።

እንዲሁም ቦሌ ክፍለ ከተማ 92 ፣የካ ክፍለ ከተማ 95 ፣ንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 83 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በ24ሰዓት ውስጥም በከተማዋ 12 ሰዎች( 12ቱም በአስክሬን ምርመራ) በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባ እስካሁን 348 ሺህ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

Exit mobile version