አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከነገ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ አይውልም አለ የገቢዎች ሚኒስቴር፡፡
የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ከባለፈው ዓመት ታሕሣሥ ወር ጀምሮ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል፡፡
ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝም ከነገ ጀምሮ ሥራ ላይ እንደማይውል ነው ሚኒስቴሩ አጽንኦት የሰጠው፡፡
በዚህ መሰረትም ከነገ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ብቻ ለአገልግሎት እንደሚውል ገልጿል፡፡
የሕትመት ጥያቄ አቅርበው የታተመላቸውን ደረሰኝ ያልወሰዱ ግብር ከፋዮች ደግሞ በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም በየታክስ ማዕከላቸው በመገኘት ደረሰኞቻቸውን እንዲረከቡ አሳስቧል።
በተመሳሳይ ግብር ከፋዮች እጃቸው ላይ የሚገኘውን የቀድሞ ደረሰኝ ለየታክስ ማዕከሎቻቸው በመመለስ የመልቀቂያ ሰነድ መውሰድ እንዳለባቸው አመልክቷል፡፡
መመሪያውን በማይተገብሩ አካላት ላይ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ርምጃ እንደሚወስድም አስገንዝቧል፡፡
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

