አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ሳተላይቶች ያመነጯቸው መረጃዎች ጉልህ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ አበርክተዋል አለ።
ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሳተላይት ኢቲ-አርኤስኤስ1 (ET-RSS1) እንዲሁም ሁለተኛው ኢቲ-ስማርት-አርኤስኤስ (ET-SMART-RSS) የተሰኙ ሁለት የመረጃ ሳተላይቶችን ወደ ሕዋ ማምጠቋ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ እንዳሉት፤ ቀደም ሲል ወደ ሕዋ የተላኩ ሁለት የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቅቀዋል።
ሳተላይቶቹ በርካታ ቴክኖሎጂያዊና ሳይንሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን አበርክተዋል ብለዋል።
በዚህም በምግብ ዋስትና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በተፈጥሮ ሃብት አያያዝ የግብርና መስኮች፣ በከተማ ፕላንና መሠረተ ልማት፣ በሀገር ሉዓላዊነትና ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳበረከቱ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በአሁኑ ወቅትም በሚቀጥለው ዓመት ታሕሣሥ ወር ላይ በምስል ጥራትና የጊዜ ቆይታ አቅም ያላት ኢቲ-አርኤስኤስ2 (ET-RSS2) የተሰኘች ሳተላይት ወደ ሕዋ ለማምጠቅ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቀጣይ የምትመጥቀው ኢቲ-አርኤስኤስ2 ሳተላይት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ በሕዋ ላይ የአምስት ዓመት ቆይታ እንዲኖራት ታሳቢ መደረጉን ነው የገለጹት።
ከዚህ ቀደም ወደ ሕዋ ከተላኩ ሳተላይቶች መረጃ የመቀበል፣ የመተንተን፣ የመቆጣጠርና የጥገና አቅም መፈጠሩን አስረድተዋል።
ሶስተኛዋን ሳተላይት ለማምጠቅ እየተደረገ የሚገኘው ጥረትም የኢትዮጵያን የሳተላይት ልማት አቅም በተግባር የሚያሳይ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

