Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግብር ከፋዮች የታተመላቸውን ደረሰኝ ወደ ታክስ ማዕከላቸው በመሄድ ሊወስዱ ይገባል – ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች ለቅጣት እንዳይዳረጉ የታተመላቸውን ደረሰኝ በታክስ ማዕከላቸው እንዲወስዱ አሳስቧል።

ልዩ መለያ ኮድ ያለው የእጅ በእጅ የሽያጭ ደረሰኝ ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ መግባቱ ተመላክቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በፍርዱ መሰረት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ነባሩን ደረሰኝ በአዲስ መቀየር አስፈልጓል።

ይህ ደረሰኝ ሕትመቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ በአይን የማይታይ ልዩ ኮድ ያለው እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር በማድረግ ሕገወጥ ደረሰኝን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በዚህም በሕጉ የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች በሙሉ ይህንን ደረሰኝ የማሳተም ግዴታ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የሒሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለባቸው ግብር ከፋዮች ደግሞ ሒሳብ መዝገብ መያዝ እስከፈለጉ ድረስ ደረሰኙን ማሳተም እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።

እንዲሁም የገቢ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሰው ገቢ የማድረግ ኃላፊነት በሕግ የተጣለባቸው ወኪሎች እና የሕትመት ድርጅቶች ለማንኛውም ወጭና ገቢ ንግድ ደረሰኝ ማሳተም እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡

በሕጉ ደረሰኝ እንዲያሳትሙ የሚገደዱት ሁሉም የፌደራል፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ግብር ከፋዮች አዲሱን ደረሰኝ ለማሳተም ግብር ወደ ሚከፍሉባቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመሄድ ጥያቄ ማቅረብ አለባቸው ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም ከደረሰኝ አቅርቦት አንጻር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ጋር ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ በሙሉ አቅም የሕትመት ሥራው እንዲከናወን በማድረግ ከዚህ በፊት የቀረበለትን የሕትመት ጥያቄ አትሞ መጨረሱን አንስተዋል።

በመሆኑም ግብር ከፋዮች ከተለያዩ ቅጣቶች ለመዳን በየቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ ታክስ ማዕከላት ወይም ወደ ማተሚያ ድርጅቱ በመሄድ የታተመላቸውን ደረሰኝ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version