አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች አልጄሪያ ከናይጄሪያ እንዲሁም ግብፅ ከኮትዲቯር ይገናኛሉ።
ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ በውድድሩ ጠንካራ አቋማቸውን በማስመልከት የምድብ ጨዋታቸውን ሙሉ በሙሉ ያሸነፉት አልጄሪያ እና ናይጄሪያ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ይፋለማሉ።
የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የሆነው ቡድን የውድድሩ አስተናጋጅ ከሆነችው ሞሮኮ ጋር በግማሽ ፍጻሜ ይገናኛሉ።
እንዲሁም ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ግብጽ ከኮትዲቯር የሚያደርጉት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ይጠበቃል።
ሁለቱ ሀገራት በሚያደርጉት ጨዋታ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን ማሊን በማሸነፍ የግማሽ ፍጻሜው ውድድሩን ከተቀላቀለችው ሴኔጋል ጋር ይጫወታሉ።

