አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የባሕር ዳር ከተማን ግቦች ፍቅረሚካኤል ዓለሙ እና ግርማ ዲሳሳ ሲያስቆጥሩ መሐመድ አበራ የመቻልን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በተመሳሳይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ መድን ይገናኛሉ።

