አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤንች ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በዓል በዛሬው ዕለት በሚዛን አማን ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
የዘመን መለወጫ በዓሉ ብሔረሰቡ ባህሉን፣ አንድነቱንና ለፈጣሪ ያለውን ምስጋና የሚያንጸባርቅበት እንደሆነ ይገለፃል።
በበዓሉ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የብሔረሰቡ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

