Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓድዋ ድል መታሰቢያን በባዶ እግሩ እየጎበኘ የሚገኘው ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታዋቂ አሜሪካዊው ዩቲዩበር እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢ ወጣት አይሾው ስፒድ ወይም ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር አዲስ አበባን እየጎበኘ ይገኛል፡፡

የ21 ዓመቱ አሜሪካዊ ዳረን ጄሰን ዋትኪንስ ጁኒየር በአሁኑ ወቅት “Speed Does Africa” የተሰኘ ጉዞ እያደረገ ሲሆን÷ አዲስ አበባ ሲደርስ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ አቀባበል አድርገውለታል።

በ20 የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረገ የአፍሪካን ባህልና ታሪክ ለዓለም እያስተዋወቀ የሚገኘው ታዋቂ ዩቲዩበሩ÷ በኬንያ በነበረው ቆይታ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ300 ሺህ በላይ አዲስ ተከታዮችን በማግኘት የዩቲዩብ ተከታዮቹን ቁጥር 48 ሚሊየን አድርሷል።

በኢትዮጵያም በርካታ ዩቱዩበሮች የአዲስ አበባ ጉብኝቱን እየተከታተሉ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ዩቲዩበሩ በአዲስ አበባ እያደረገ ያለውን ጉብኝት በዩቲዩብ ገጹ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ሲሆን÷ ከ191 ሺህ በላይ ሰዎች የቀጥታ ስርጭቱን እየተከታተሉ መሆናቸውን ተመልክተናል፡፡

ታዋቂ ዩቲዩበሩ በአሁነ ሰዓት የዓድዋ ድል መታሰቢያን በባዶ እግሩ እየጎበኘ ይገኛል።

Exit mobile version