Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት ውድድር በመጪው ቅዳሜ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተወዳጁ ፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር 12ኛ ሳምንት በመጪው ቅዳሜ ቀጥሎ ሲካሄድ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል።

በዕለቱ ዳዊት ኪ/ማርያም፣ ታፈረ አሰፋ፣ አሮን ሀይሉ፣ አቤል ጌትነት እና ግዛቸው አማረ በቀጥታ ስርጭት ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዕለት አቀራረብን መሰረት የሚያደርገው የፋና ላምሮት ውድድር በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖረዋል።

ይሄን ወደ ፍጻሜ ለማለፍ የሚካሄደውን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት በመጪው ቅዳሜ ከ6:00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሁለቱም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ በፋና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች፣ በፋና ዩቲዩብ እና በ www.fanamc.com ይከታተሉ።

እንዲሁም በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናኑ የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።

Exit mobile version