Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፋር ባህላዊ ሕግን ‘ማድዓ’ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ባህላዊ ሕግን (ማድዓ) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እየተሰራ ነው።

የማድዓ ባህላዊ ሕግን በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከየካቲት 3 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሕዝባዊ ኮንፍረንስ ይካሄዳል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሀሚድ ዱላ እንዳሉት፤ ኮንፍረንሱ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በጋራ ያዘጋጁት ነው።

በኮንፍረንሱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎች እንዲሁም የጅቡቲ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ሱልጣኖች እና የጎሳ መሪዎች ይሳተፋሉ ብለዋል።

የክልሉ የቋንቋ ባህልና ታሪክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀቢብ መሀመድ በበኩላቸው፤ ኮንፍረንሱ ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ቀጣናዊ ትስስርን ያጠናክራል ሲሉ ተናግረዋል።

የማድዓ ባህላዊ ሕግን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የዓለም ሀብት እንዲሆን ከማስቻል ባለፈ በክልሉ ያለውን የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘመን በየነ

Exit mobile version