Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአይሾው ስፒድ የኢትዮጵያ ቆይታ የሚሊየኖች ዐይን ወደ አዲስ አበባ እንዲሳብ አድርጓል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ በኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት በመላው ዓለም የሚሊየኖች ዐይን ወደ አዲስ አበባ እንዲሳብ አደርጓል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጉብኝቱ ከተማችን ያላትን የቆየና የከበረ የእንግዳ ተቀባይነት ባህልና የከተማችንን ፅዳትና ውበት ለዓለም የገለጠ ስኬታማ መርሐ ግብር ነበር ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል ያሉት ከንቲባዋ፥ ወደፊትም ብዙዎችን ወደ ሀገራችን እንደሚስብ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሁነቱ እስካሁንም መነጋገሪያነቱ መቀጠሉን ገልጸው፥  መርሐ ግብሩን ላስተባበሩ ሀገር ወዳድና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ለፌደራልና ለአዲስ አበባ መንግስታዊና የግል ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተለይም የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ ይሳቃል ኢንተርቴይመንትና ሌሎች ባላድርሻ አካላት ላሳዩት ቅንጅት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version