Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጥምቀትን በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥምር የፀጥታና የደህንነት ግብረ ኃይል የከተራ እና የጥምቀት በዓል በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደ ስራ ተገብቷል አለ።

በግብረ ኃይሉ የተደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅት የፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፋንታ እንዳሉት፤ በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል መላዉ የፀጥታ ኃይል አመራር እና አባላት ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ የስራ መመሪያ ሰጥቷል።

በበዓሉ ላይ ኃይማኖታዊ ያልሆኑ መልዕክቶች፣ በዓሉን የማይመጥኑና በህግ የተከለከሉ ነገሮችን በዓሉ ወደሚከበርባቸዉ ቦታዎች ይዞ መምጣት የተከለከለ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው፤ ለጋራ ደህንነት ሲባል የፀጥታ ኃይሉ ለሚያከናውነው የፀጥታ ስራ ህብረተሰቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ቀደም ብሎ ውይይት መደረጉን አስታውሰው፤ ህብረተሰቡ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የበኩሉን እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መሰራቱን የገለጹት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ ናቸው።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል።

በተጨማሪም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

Exit mobile version