አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቻል አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የመቻልን ግቦች ቸርነት ጉግሳ በፍጹም ቅጣት ምት እና ቻርለስ ሙሲጌ በጨዋታ አስቆጥረዋል።
የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ቀን 10 ሰዓት ላይ በተመሳሳይ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይገናኛል።
በተጨማሪም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ መካሄድ የጀመረ ሲሆን÷ አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ስታዲየም ይጫወታሉ።

