አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ ግብጽን በማሸነፍ 3ኛውን ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች ።
ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ መደበኛ የጨዋታ ጊዜ አልቆ በመለያ ምት ናይጄሪያ ግብጽን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
ይህንን ውጤት ተከትሎም ናይጄሪያ በውድድሩ 3ኛ ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ግብጽ 4ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።
የአፍሪካ ዋንጫ በነገው ዕለት ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ ከሴኔጋል ጋር ለዋንጫው ይፋለማሉ።

