አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥምቀት ከተራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባህር በማቅናት ላይ ሲሆኑ የተለያዩ ሐይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከናወኑ ይገኛል።
በርካታ ምዕመናን እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎችን ጨምሮ የበዓሉ ታዳሚዎችም ታቦታትን አጅበው በመጓዝ ላይ ናቸው።

