Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የከተራ በዓልን በጎንደር በመታደማችን ልዩ ደስታ ተሰምቶናል – የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቱሪስቶች በከተራ በዓል በመታደማችን ልዩ ደስታ ተሰምቶናል አሉ።

የጥምቀት ከተራ በዓል በጎንደር ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

አሁን ላይ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው የጥምቀት ሥነ ሥርዓት በሚከናወንበት ባሕረ ጥምቀት ደርሰዋል።

በከተራ በዓል አከባባር ላይ የታደሙት የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ፥ የከተራ በዓልን በጎንደር በመታደማቸው ልዩ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

በአከባባር ሥነ ሥርዓቱ የተመለከቷቸው ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች እንዳስገረሟቸው አውስተዋል።

በተለይም ታቦታት ታጅበው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ሲያቀኑ የሚከናወኑ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ክዋኔዎች ልዩ ስሜት እንደሚፈጥሩ ነው ያብራሩት።

የሕዝቡ እንግዳ ተቀባይነት፣ አብሮነት እና መተሳሰብ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፥ የከተማዋ ውበት ለበዓሉ ድምቀት መስጠቱን ተናግረዋል።

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version