Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተኪ ምርቶችን በማምረት ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ማዳን የቻሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን በማምረት ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ማዳን ቻሉ።

የከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከባለሃብቶችና የዳያስፖራ አባላት ጋር በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዙሪያ የሚመክር የኢንቨስትመንት ፎረም እያካሄደ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጎንደር ያላትን ፀጋና ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንዲትችል በትኩረት እየተሰራ ነው።

በኢንቨስትመንት ዘርፍ ጎንደር የተሻለ እድል ማግኘቷን ገልጸው÷ አሁን ላይ በቱሪዝምና በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትልቅ አቅም እንዳላት አብራርተዋል።

ጎንደር ሰባት ዓለም አቀፍ ቅርሶች ያሏት በመሆኑ የቱሪዝም ገቢዋን ለማሳደግ ከምትጠቀምባቸው መስኮች ቀዳሚ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ባለፉት ስድስት ወራት ለ142 ባለሃብቶች ፈቃድ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን÷ በዚህም ከ12 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል ማግኘታቸው ተመላክቷል።

በከተማዋ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አሁን ላይ 72 በመቶ ማድረስ የተቻለ ሲሆን÷ ተኪ ምርቶችን በማምረት ከ35 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ማንዛሪ ማዳን መቻሉ ተገልጿል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

Exit mobile version