Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ግብ ኮንኮኒ ሀፊዝ ሲያስቆጥር÷ ሄኖክ አዱኛ ደግሞ የሸገር ከተማን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

የሊጉ በርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ በተመሳሳይ ስታዲየም 10 ሰዓት ላይ ምድረ ገነት ሽረ እና አርባ ምንጭ ከተማ ይገናኛሉ።

እንዲሁም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዳማ ከተማ ሲገናኙ 12 ሰዓት ላይ በተመሳሳይ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማ ከነገሌ አርሲ ይጫወታሉ።

Exit mobile version