Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ያላትን ተሳትፎ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ያላትን ተሳትፎ በማጠናከር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴዋን አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ሃይማኖት እሸቱ (ዶ/ር)።

ተመራማሪዋ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በርካታ ሀገራት ተቀራርበው በመምከርና በመደራደር ድንበር ተሻጋሪ ችግሮችን ለመፍታትና የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያስችል ወሳኝ መድረክ ነው።

ይህ ዓይነቱ ትብብር በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የኃይል ክፍፍሎች እንዳይፈጠሩ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናዊ ትብብር እና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ረጅም ታሪክና የማይቋረጥ ዐሻራ ያላት ሀገር መሆኗን አንስተው÷ ሁልጊዜም በፍትሃዊነትና በእኩልነት መርህ እንደምታምንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ በአንድ ወገን ላይ ብቻ ከመወሰን ይልቅ አጋርነትን በማስፋት ላይ ያተኮረ ነው ያሉት ተመራማሪዋ÷ ይህም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢኮኖሚ ትስስር መፈጠር ለሀገር ዕድገት ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥም መሰረታዊ ዋስትና እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

በሔለን ታደሰ

Exit mobile version