Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በሁሉም ዘርፍ የታቀዱ ሥራዎች በአማካይ ከ95 በመቶ በላይ ተሳክተዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተለወጠ የሥራ ባህል፣ ነዋሪዎችን እና የልማት አጋሮችን በማስተባበር በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ ሥራዎችን በአማካይ 95 ነጥብ 3 በመቶ ማሳካት ተችሏል አሉ።
የመዲናዋ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የመንግሥትና የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፍ የታቀዱ ሥራዎችን በአማካይ 95 ነጥብ 3 በመቶ እንዲሳካ ላስቻሉ አመራሮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም የልማት አጋሮችን ምስጋና አቅርበዋል።
የላቀ ውጤት ብናስመዘግብም በተቋማት ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
መድረኩ ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ተጨማሪ አቅምና ተሞክሮ የምንሰንቅበት እንዲሁም የከተማችንን ነዋሪዎች በተሻለ ትጋትና ታማኝነት ለማገልገል የምንዘጋጅበት ይሆናል ሲሉም አመልክተዋል።
Exit mobile version