Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአውሮፕላን ማረፊያው አዲስ ተርሚናል በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል አሉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተርሚናሉን የግንባታ ሂደት በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡

ተርሚናሉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ፣ ለተሳፋሪዎች ምቹና ለዕይታ ተስማሚ ሆኖ እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም መሰረት በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመልክተዋል፡፡

Exit mobile version