Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ተከትሎ የደስታ ማብሰሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወላይታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ጊፋታ” በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን ተከትሎ ሀገራዊ የደስታ ማብሰሪያ መርሐ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የማብሰሪያ መርሐ ግብሩ “የጊፋታ ብስራቶች ለሕዝቦች ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ጊፋታ በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን÷ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣና የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ በዓል ነው፡፡

በማቴዎስ ፈለቀ

Exit mobile version