Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበ ነው – የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል በየዓመቱ ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበ ነው አሉ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳው።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቢሾፍቱ በተካሄደው የኢፌዴሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል።

በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም የአሜሪካን አየር ኃይል ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስረታ ጊዜ ጀምሮ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተው÷ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ሴክሬተሪ ማርክ ሩቢዮን በመወከል የክብረ በዓሉ አካል በመሆኔ ላቅ ያለ ደስታና ክብር ተሰምቶኛል ብለዋል።

በቀጣናው ኢትዮጵያ ወሳኝ ሀገር ናት ያሉት ክርስቶፈር÷ በቀጣናው መረጋጋትን በጋራ ዕቅድ እየተመራን ስኬታማ ተግባራትን አከናውነናል ሲሉም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ ለማፋጠን የአሜሪካ ድጋፍና ተሳትፎ የማሳደግ ፍላጎት መኖሩን አንስተዋል።

ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው÷ ባዩት የአየር ላይ ትርዒት መደሰታቸውንም ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ ክርስቶፈር ላንዳውን ጨምሮ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ተገኝተዋል።

በመራኦል ከድር

Exit mobile version