አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ ሕብረት እና አሜሪካ በመሠረተ ልማት፣ በሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ በዛሬው ዕለት ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና ከአሜሪካ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እንዳሉት፤ የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ጉብኝት በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ትብብር ወሳኝ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
በመከባበር፣ በጋራ ጥቅም፣ ሰላም እና መረጋጋት እና ብልጽግናን በማስፈን ላይ የተመረተው የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ህብረቱ ያለውን ቁርጠኝነትን አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች ስትራቴጂካዊ በሆኑ የመሠረተ ልማት እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

