Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሉካስ ፓኩኤታ ፍላሚንጎን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዝላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሉካስ ፓኩኤታ የሃገሩን ክለብ ፍላሚንጎን በ41 ሚሊዮን ዩሮ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል፡፡

የ28 አመቱ ተጫዋች በ2022 ከፈረንሳዩ ሊዮን ዌስትሃም ዩናይትድን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

ሉካስ ፓኩኤታ በክለቡ እንዲቆይ ግፊት ብናደርግም በተጫዋቹ የቤተሰብ እና ሌሎች ጉዳዮች መልቀቂያውን ተቀብለናል ብሏል ክለቡ፡፡

በዚህም ተጫዋቹ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ዝውውሩን እንዲያጠናቅቅ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡

መዶሻዎቹ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ደረጃ በመያዝ በወራጅ ቀጠና ስፍራ ይገኛሉ፡፡

Exit mobile version