አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ “የአንበሶቹ ሰማይ – ኢትዮጵያ” በሚል በቀረበው የአየር ላይ ትርኢት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አብራሪዎች የዕውቅናና ምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንዳሉት÷ አብራሪዎቹ በትርዒቱ ወቅት ያሳዩት የላቀ ብቃትና ጥበብ ከመደበኛው ወታደራዊ ተግባር ባሻገር የተቋሙን ዝግጁነትና የቴክኖሎጂ የበላይነት ለዓለም ያስመሰከረ ነው።
ዕውቅናው አብራሪዎቹ ለሀገር ሉዓላዊነትና የአየር የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ተጋድሎ የሚዘክር ከመሆኑም በላይ ለተቋሙ ቀጣይ ትውልድ ትልቅ የሞራል መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

