Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 የፍጻሜ ውድድር በነገው ዕለት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሦስት ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው ፋና ላምሮት የምዕራፍ 21 የፍጻሜ ውድድር በነገው ዕለት ይካሄዳል።

አቤል ጌትነት፣ አሮን ሀይሉ፣ ግዛቸው አማረ እና ታፈረ አሰፋ የፍጻሜ ውድድሩ ተፋላሚዎች ሲሆኑ÷ በሦስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከኮከብ ባንድ ጋር ያቀርባሉ፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተወዳዳሪዎቹ የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።

በዚህም መሰረት ውድድሩን አንደኛ ደረጃ በመያዝ የሚያጠናቅቅ 400 ሺህ ብር፣ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ደግሞ የ300 ሺህ፣ የ200 ሺህ እና የ100 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ ይሆናሉ፡፡

አራቱም የምዕራፍ 21 የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ለ6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ላይ አንድ ተወዳጅ ሙዚቀኛ በክብር እንግድነት ይገኛል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አድማጭ ተመልካቾች የቅዳሜውን የፍጻሜ ውድድር በሁለቱም የፋና ቴሌቪዥን ቻናሎች እንዲሁም በፋና ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲከታተሉ ይጋብዛል፡፡

ነገ ቅዳሜ ከ6 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩን በቀጥታ ሥርጭት በመከታተል በዕለቱ የሚገለጸውን የተወዳዳሪዎችን ኮድ በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።

Exit mobile version