Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአየር ኃይል የምስረታ በዓል በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል።

ለክብረ በዓሉ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የአየር ኃይል የሰራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች ነው ልዩ የምስጋና መርሐ ግብር የተካሄደው።

የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት÷ የበዓሉ አከባበር በዓለም ፊት ኢትዮጵያን ያኮራ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።

ተቋሙ በ90 ዓመታት የጉዞ ታሪኩ ያስመዘገባቸው ስኬቶች የፅናትና የሀገር ፍቅር ውጤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ አባላቱ እያሳዩት ያለው ቁርጠኝነት ለሀገር ሉዓላዊነት አስተማማኝ ዋስትና መሆኑን ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

የ90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አየር ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቴክኖሎጂ የዘመነ፣ በሰው ኃይል የሰለጠነና በአንድነት የተሳሰረ መሆኑን ዳግም ለዓለም በተግባር ያሳየበት ክስተት ሆኖ መጠናቀቁንም አመልክተዋል።

Exit mobile version