አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 17ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል “አዲስ አበባ የባህል እና ፈጠራ ሞዛይክ” በሚል መሪ ሃሳብ በኤግዚቢሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።
በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ፌስቲቫሉ የሕብረተሰቡን ወግና ባህል እንዲሁም እሴት ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ እድል የሚፈጥር ነው።
የከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫሉ እስከ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በፌቨን ቢሻው

