አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፊታችን ማክስኞ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡
በተጨማሪም ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

