Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቷል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቤል ታደሰ እንዳሉት ÷ በግማሽ ዓመቱ የተገኘው ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት በዓመቱ ከተገኘው የበለጠ ነው፡፡

የተቋሙን የአሰራር ሥርዓት ለማዘመንና ለማሻሻል የሰው ሃይል አቅምን ማጠናከርና የአገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ላይ በትኩረት መሰራቱን አመልክተዋል፡፡

የድርጅቱ የገበያ ድርሻ አሁን ላይ 45 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን የገለጹት አቶ አቤል÷ ለዘንድሮው የላቀ አፈጻጸም ማሻሻያው ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል፡፡

50 ዓመታትን በመድን አገልግሎት የዘለቀው ድርጅቱ ዘርፉን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦው እያበረከተ እንደሚገኝ አውስተዋል፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

Exit mobile version