Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሁሉም ተቋማት ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲገቡ እየተሰራ ነው – አለምፀሐይ ጳውሎስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማፋጠን ሁሉም ተቋማት ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲገቡ እየተሰራ ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ 14 ተቋማት የ2018 በጀት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ተገምግሟል፡፡

ሚኒስትሯ በግምገማ መድረኩ ተቋማት የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሪፎርም በመምራት ለብልጽግና ጉዞ እና ዘላቂ ሀገራዊ ልማት እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረቻቸውን ዲጂታል 2030፣ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና፣ የፋይዳ ዲጂታል እና መሰል የሪፎርም ኢኒሼቲቮችን በታቀደው ልክ በመተግበር ለዘላቂ ብልጽግና መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የተጀመሩ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ እና ለብልጽግና ተደማሪ አቅም ለመፍጠር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት አርዓያ ሊሆኑ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ለሌብነት እና ምዝበራ የተጋለጡ ተቋማት ላይ የዲጂታል አሰራርን በማጠናከር አገልግሎቶችን በልዩ ትኩረት በመምራትና ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲገቡ በማድረግ እርካታን ማሳደግ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

Exit mobile version