በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዋትሳፕ (WhatsApp) አካውንት ጠለፋ በስፋት እየተለመደ የመጣና ብዙዎችን ለከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እየዳረገ ያለ ችግር ነው።
ይህንን ስጋት ለመከላከልና የሳይበር ደህንነትዎን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ዋና ዋና የጥንቃቄ የጥንቃቄ እርምጃዎች መተግበር አስፈላጊ ነው።
ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን #Two_Step_Verification ማተግበር፦ይህ ዘዴ አካውንትዎ እንዳይጠለፍ የሚያደርግ ቁልፍ የመከላከያ ጋሻ ነው። ይህን ካደረጉ ጠላፊው የእርስዎ ሲም ካርድ ቢኖረው እንኳ ያለ እርስዎ ሚስጥራዊ ቁጥር መግባት አይችልም።
የማረጋገጫ ኮድ #Verification_Code ለማንም አለመስጠት፦ዋትሳፕ በኤስኤምኤስ (SMS) የሚልክልዎትን ባለ 6 አሃዝ ኮድ በፍጹም ለማንም አያጋሩ።
አጠራጣሪ ሊንኮችን #Links አለመንካት፦ በግሩፖች ወይም በግል የሚላኩ “ነፃ የኢንተርኔት ጥቅል”፣ “የስራ ዕድል” ወይም “የቴሌግራም/ዋትሳፕ ስጦታ” የሚሉ ሊንኮች ማጥመጃ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህን ሊንኮች ሲነኩ ስልክዎ ላይ ቫይረስ ሊጭኑ ወይም መረጃዎን ሊሰርቁ ይችላሉ።
የዋትሳፕ ድረ-ገጽ #WhatsApp_Web አጠቃቀምን መከታተል፦ ኮምፒውተር ላይ ዋትሳፕ ተጠቅመው ሲጨርሱ ሁልጊዜ #Log_out ማድረጋቸውን ያረጋግጡ፤ እንዲሁም #Linked_Devices የሚለውን ክፍል በመግባት እርስዎ የማያውቁት ሌላ መሣሪያ #Device ተገናኝቶ ከሆነ Log out በማድረግ ግንኙነቱን ያቋርጡ።
ፎቶ እና መረጃን መደበቅ፦ጠላፊዎች የእርስዎን ፎቶ እና ስም በመጠቀም አዲስ አካውንት ከፍተው ቤተሰቦችዎን “ገንዘብ ቸግሮኝ ነዉ ላኩልኝ” ብለው ሊያታልሉ ይችላሉ። በመሆኑም Settings > Privacy በመግባት Profile Photo እና About የሚሉትን ወደ “My Contacts” ብቻ ይቀይሩ።

