አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት ተቋርጧል አለ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፡፡
የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት የተቋረጠበት ምክንያትም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1. በየአካባቢው የሚገኙ የኢንተርኔት እና ሕትመት ቤቶች ጥራት በሌላቸው ካርዶች እያተሙ በመሆኑ፣
2. የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በፎቶሾፕ እያስመሰሉ በመስራት የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችን እያጭበረበሩ ያሉ አታሚዎች በስፋት መታየታቸው፣
3. ከከተማ ራቅ ብለው የሚኖሩና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ዜጎች ትክክለኛ ባልሆነ የካርድ ሕትመት እየታለሉ ፤ ገንዘብና ጊዜያቸውን ከመጭበርበራቸው ባሻገር የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ እያደረገ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡
ስለሆነም ዜጎች የኢ-ፋይዳ አማራጭ ሲፈልጉ የ”Fayda ID” ሞባይል መተግበሪያ ላይ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አመልክቷል፡፡

