አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በስብሰባው የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

