Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

በፈረንጆቹ 2025 በዓለም ላይ 10 ፈጣን ዕድገት የተመዘገበባቸው ሀገራት መካከል አምስቱ አፍሪካ ውስጥ ናቸው። ይህ የሚያሳየው ምንም እንኳን ቁጥሩ መበራከት ቢኖርበትም ለሚቀጥሉት 25 እና 30 ዓመታት ይሁነኝ ብለን ከተጋን አሁን ወደ እስያ ያመራው ዕድገት እና ብልጽግና ወደ አፍሪካ ለመምጣት ሰፊ እድል እንዳለው ያሳያል፣
ይህ የሚሆነው ገብቶን አውቀን አስበንበት ልጆቻችን ላይ ከሰራን ነው፤ የምንሰራው ሁሉ ዛሬውኑ ውጤት የሚታይበት አይደለም፣
ኢትዮጵያ ቦታዋ የት ነው ከተባለ ነዳጅ ከማያመርቱ 10 ሀገራት ከቀዳሚዎቹ አንዷ ናት፤ አምና የተመዘገበው 9 ነጥብ 2 በመቶ ነው፤ ይህ ዳታ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ነው፣
አምና የተመዘገበው ዕድገት ብቻ ሳይሆን ዘንድሮ እንደ አይኤምኤፍ ትንበያ ከሆነ አፍሪካ በዘመናዊ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስያ የላቀ ዕድገት ሊመዘገብ እንደሚችል ተንብዩአል፣
የኢትዮጵያን ብንወስድ በዚህ ዓመት የነበረን ዕቅድ እና ለፓርላማ ያስገባነው 9 ነጥብ 2 በመቶ እድገት እናመጣለን ብለን ነበር፤ ነገር ግን የስድስት ወር ውጤት ገምግመን ከዚያ በላይ ማደግ ስለምንችል ወደ 10 ነጥብ 2 በመቶ እናሻሽለው ነው ያልነው፣
አይኤምኤፍ የ2026 የኢትዮጵያ ዕድገት 9 ነጥብ 3 በመቶ ይሆናል ብሎ ነው የተነበየው፤ እኛ ካቀድነው በ0.1 በመቶ የተሻለ ማለት ነው፤ አሁን ካሰብነው 10 ነጥብ 2 ደግሞ ከ1 በመቶ በታች በእኛ እና በአይኤምኤፍ መካከል የትንበያ ልዩነት አለ።
በሶስና አለማየሁ
Exit mobile version