በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች sosina alemayehu 3 hours ago የኢትዮጵያ አየር ሃይል በተለያየ ስም የሚጠሩ ከመቶ በላይ አውሮፕላኖች አለው፣ ተቋም የምንገነባው ለምንድነው፣ ባንዳው ከማቁሰል አያልፍም ዝግጅታችን ለቁስል ሳይሆን ምሰሶ የሚገዳደሩ ኃይሎች ከመጡ ኢትዮጵያን ለማጽናት እና ለማስቀጠል ነው፣ ጠላቶቻችን ለባንዳዎች 10 ብር ደመወዝ መክፈል የሚችሉ ከሆነ እኛ ለኢትዮጵያ መቶ ብር መክፈል መቻል አለብን፤ ከእነሱ የበለጠ ሃብት ካላመነጨን በስተቀር በሃብት፣ በዲፕሎማሲ በሚዲያ ምክንያት ጫና ያመጣሉ፣ የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት የውስጥ ጉዳዩን መፍታት ሳይችል ቀርቶ የቀይ ባህር ጉዳይን ያነሳል ብሎ ይከሳል፤ የውስጥ ጉዳያችን ላይ በርበሬ አቅራቢው አማሳዩ ሳለ ተቀምጦ ሳለ ውስጥ እና ውጪ የሚለው ጉዳይ እንዴት ይሆናል? መፍትሄው መብቃት ነው! ኢትዮጵያን መጉዳት የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ ገንዘብ ፋይናንስ ያደርጋሉ ኢትዮጵያን ግን አይችሏትም፤ ገንዘባቸውን ያፈሳሉ፣ ይከስራሉ እኛ ጉዟችንን እንቀጥላለን፣ የውይይት በር ክፍት ማድረግ አለብን ዛሬ ባንዳ የተባለ ሰው ልብ ገዝቶ በቃኝ ካለ ሁሌ ክፍት መሆን አለብን፤ ቂም መያዝ አያስፈልግም የግል ጉዳይ አይደለም፤ የሀገር ጉዳይ ነው፣ ጉዳያችን ስም አይደለም፤ ጉዳያችን ስድብ አይደልም፤ ለእኛ ጉዳያችን ኢትዮጵያ ናት፣ ማንም ሰው ለሰላም ዝግጁ እስከሆነ ድረስ ለመወያየት እና ለይቅርታ ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። በሶስና አለማየሁ