Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ104 ሺህ በላይ ሰዎች የኮደርስ ስልጠና ምስክር ወረቀት ወሰዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 104 ሺህ 700 ሰዎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ምስክር ወረቀት ወስደዋል።

የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይለማርያም ተስፋዬ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎትና ዕውቀትን ለማሳደግ ክልሉ ሰፊ ዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል።

በዚህም መሰረት የ5 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ የስልጠና ዕድል ለመጠቀም የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በፕሮግራሚንግ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ዳታ ሳይንስ እና በአንድሮይድ ልማት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው÷ ስልጠናው የተጀመረውን የዲጂታል ስርዓት ሽግግር ውጤታማ ለማድረግ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

በክልሉ 184 ሺህ 393 ሰዎች ተመዝግበው ስልጠናውን እየተከታተሉ እንደሆነ አንስተው÷ እስካሁን 104 ሺህ 700 ሰዎች ስልጠናውን በማጠናቀቅ ምስክር ወረቀት ወስደዋል ነው ያሉት።

የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠናው ውጤታማ እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት እየሰሩ እንደሆነም አመልክተዋል።

በአቢይ ጌታሁን

Exit mobile version