Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀዋሳ ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ የሀዋሳ ከተማን ግቦች ሽመልስ በቀለ እና ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አገናኝተዋል።

ቀደም ብለው በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ሀዲያ ሆሳዕና እና መቻል 1 ለ 1 አቻ ሲለያዩ÷ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ሸገር ከተማ ከምድረ ገነት ሽረ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

Exit mobile version