አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታውን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ማስጀመራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መንግሥት የዜጎችን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እንሰራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።

