Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 በአጋሮ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት …

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አጋሮ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

ማዕከሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው በዛሬው ዕለት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው፡፡

መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች የሚገባቸውን አገልግሎት በአንድ ቦታ እንዲያገኙ እያስቻለ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ  ነመራ ቡሊ በበኩላቸው÷ በክልሉ የቅሬታ ምንጭ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ኮከቤ ዲዳ÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዚህ ቀደም ተገልጋዩ ያጋጥመው የነበረውን እንግልት እንደሚያስቀርና አገልግሎት አሰጣጥን እንደሚያቀላጥፍ ተናግረዋል።

በወርቅአፈራሁ ያለው

Exit mobile version