Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ልጆችን የትምህርት ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክት…

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሌይፉል ኢዱኬሽን ፓዝዌይስ ኢትዮጵያ ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ልጆችን የትምህርት እድል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡

የፕሌይፉል ኢዱኬሽን ፓዝዌይስ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ይልቃል ቻላቸው እንዳሉት÷ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነትን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡

በዚህ መሰረትም ፕሌይፉል ኢዱኬሽን ፓዝዌይስ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሚተገበር የሶስት ዓመት የትምህት ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ በተለይም በግጭት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ልጆች የትምህርት እድል እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚተገበረው ፕሮጀክቱ ፤ 150 ሺህ 620 ከትምህርት ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በዓለም አቀፉ ግብረ ሰናይ ድርጅት (አይ አር ሲ)፣ በሉሚነስ ፈንድ፣ በኢማኑኤል ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን፣ በትግራይ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን እና በሕረብተሰቡ ትብብር ነው የሚተገበረው፡፡

መድረኩ ፕሮጀክቱ መጀመሩን ከማስተዋወቀ ባለፈ ለስራው ስኬታማነት እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ያለው ሚና እና ሃላፊነት ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በ9 ሚሊየን 980 ሺህ ዶላር ወጪ የሚተገበረው ፕሮጀክቱ ግጭት ባለባቸውና በሌለባቸው አካባቢዎች ጨዋታን መሰረት ያደረገ የትምህርት ዘዴን በመጠቀም ለማስተማር እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ እና ሌሎች አካላት ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት በቅንጅት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version