Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

ሰንደርላንድን በኤምሬትስ ስታዲየም ያስተናገዱት አርሰናሎች 3 ለ 0 በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።

በጨዋታው የመድፈኞቹን ግቦች ማርቲን ዙቢሜንዲ እና ቪክቶር ዮኮሬሽ (2) ከመረብ አገናኝተዋል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በተካሄደው የቼልሲ እና ዎልቭስ ጨዋታ ቼልሲ 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋታው የቼልሲን ሦስቱንም ግቦች ኮል ፓልመር (ሁለቱን በፍጹም ቅጣት ምት) ከመረብ ሲያሳርፍ የወልቭስን ብቸኛ ግብ ቶሉዋላሴ አሮኮዳሬ አስቆጥሯል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች አስቶንቪላ እና ቦርንማውዝን 1 ለ 1፣ ኤቨርተን ፉልሃምን 2 ለ 1፣ ዌስትሃም በርንሌይን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

Exit mobile version