Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሕንድ አጋርነት ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራች ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሕንድ አጋርነት ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራች ነው አሉ የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)።

በአፍሪካ ሕብረት የልማት ኤጀንሲ (AUDA-NEPAD) እና ማሕበራዊ እና የልማት ለውጥ ማዕከል (CSEP) አማካኝነት የተዘጋጀ የአፍሪካ ሕንድ የልማት አመላካች የጥናት ውጤት ይፋ ሆኗል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሕንድ አጋርነት ተጨባጭ ስራዎችን በመስራት ላይ ትገኛለች።

ኢትዮጵያ የሕንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ተቀብላ ማስተናገዷን አስታውሰው÷ ይህም በሕንድ እና አፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳድጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የሁለቱን ወገኖችና የደቡብ ለደቡብ ግንኙነት የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል።

ይፋ የተደረገው ጥናት የፋይናንስ ግኝት እድሎችን ለማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስፋት እና አጋርነትን ለማሳደግ ወሳኝ ስለመሆኑም አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር እና የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ አኒል ኩማር ራይ በበኩላቸው÷ በጥናቱ የተገኙ ውጤቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር መስራት ይገባል ብለዋል።

በአፍሪካ አጀንዳ 2063 ላይ በጋራ ለመስራት ፍላጎት መኖሩን ጠቅሰው÷ ሕንድ ለልማት መሪ አድርጋ የተጠቀመችው የተቋማት ግንባታ ላይ በልዩ ትኩረትና ትብብር እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

በለይኩን ዓለም

Exit mobile version